የቪክቶሪያ መንበረ ብርሃን ዳግማዊ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን
የዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት

” ንዑ ፡ ደቂቅየ ፡ ወስምዑኒ ። ፈሪሀ ፡ እግዚአብሔር ፡ እምሀርክሙ ።” መዝሙር ዘዳዊት ፴፬፥ ፲፩

ርዕይ

ሕጻናትና ወጣቶች የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን ሕግና ሥርዓት አውቀውና አክብረው በሃይማኖትና በመልካም ሥነ ምግባር ጸንተው ሲኖሩ ማየት።

ተልዕኮ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መሠረታዊ ትምህርት የበለጸጉ በመልካም ሥነ ምግባር የታነጹ ለቤተክርቲያን ተተኪዎችን ማፍራት፡፡

እሴቶች

ወቅቱን ያገናዘቡ መንፈሳዊ የማስተማሪያ ዘዴዎችን በመጠቀም ሕጻናትና ወጣቶች የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዓተ እምነትና ክርስቲያናዊ ትውፊት እንዲያውቁና እንዲጠብቁ ማስተማር።

ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት

“ለነገ የቤተ ክርስቲያን ገጽታ የምትጨነቁ ከኾነ ዛሬ የሰንበት ትምህርት ቤትን አገልግሎት በልባችኹ አኑሩ”

– ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ

በብጹዕ አባ ማትያስ ከፍተኛ ድጋፍ አድራጊነት በደብሩ እውቅና ተሰጥቶት  በጥር 26 ቀን ፳፲፲፪ ዓ.ም በይፋ ተመስርቷል፡፡ በዚህም መሰረት ስያሜውን ብጹዕነታቸው ባመላከቱት መሠረት « የቪክቶሪያ መንበረ ብርሃን ዳግማዊ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት» ተብሎ ተሰይሟል፡፡

ሰንበት ት/ቤቱ በአሁኑ ወቅት የተጣለበትን መንፈሳዊ አደራ ለመወጣት ልዩ ልዩ መንፈሳዊ አገልግሎትን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ለሕጻናት፣ ታዳጊዎችና ወጣቶች የመዝሙር፣ መጽሐፍ ቅዱስና የቋንቋ ትምህርቶች በማዘጋጀት ቅዳሜ እና እሑድ በመደበኛነት እየሰጠ ይገኛል፡፡ በሚከተሉት የአገልግሎት ክፍሎች ማካኝነት ልዩ ልዩ መንፈሳዊ አገልግሎትን እየሰጠ ይገኛል፡፡ 

የሰንበት ት/ቤቱ የትምህርት ክፍሎች

ሕጻናት (ከ፰ ዓመት በታች)

ታዳጊዎች (ከ፲፪ ዓመት በታች)
ወጣቶች (ከ፲፫ ዓመት በላይ)

አመራሮች

ለሚኖራችኹ አስተያየት የሰንበት ትምህርት ቤቱን ጽ/ቤት ኤሜይ SundaySchool@stgabrieleotcvictoria.org  ይጠቀሙ።