የኮሮና ቫይረስን (COVID-19) አስመልክቶ ከሰበካ ጉባኤ የተሰጠ ማሳሰቢያ ሰኔ ፲፮
የኮሮና ቫይረስን (COVID-19) አስመልክቶ ከሰበካ ጉባኤ የተሰጠ ማሳሰቢያ
“ነገር ግን ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን”
፩ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ፲፬፥ ፵
ከሁሉም አስቀድመን በየዘመናችን ሁሉ ለጠበቀንና በነገር ሁሉ ለረዳን የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ምስጋናችንን እናቀርባለን። የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤልና ይልቁንም የሰማዕቱ ቅዱስ ቂርቆስ ቃልኪዳንና ጸሎት ተራድቶን የአጥቢያችን የአምልኮ ሥርዓት ሳይታጎልና የምዕመናንም አንድነት እየጠነከረ ለዚህ ጊዜ ደርሰናል። አሁን ላይ በመንግስት የመልሶ አገልጎት መጀመር እቅድ (restart Plan) ምክንያት ምዕመናን ወደ ቤተ ክርስቲያን እየመጡ ለምስጋናና ለአምልኮ መሰጠታቸውን እናደንቃለን። በዚሁ አጋጣሚ በተለያዩ ጊዜያት ምዕመናን ለሚሰጡት አስተያየትና ድጋፍ አክብሮታችንን እየገለጽን በቀጣይም በአገልግሎታችን ውስጥ የበለጠ ጥንቃቄ ለማደርግና የጠላት ዲያቢሎስን ፈተኛዎች ለመታገል እንዲረዳን እንዲሁም የግዛቱ ጤና መኮንን የሚሰጡትን መመሪያ ተግባራዊ ለማድረግ እንዲያስችለን የሚከተሉትን ማሳሰቢያዎች ለማስተላለፍ እንፈልጋለን።
- አሁንም ቢሆን የሁለት ሜትር አካላዊ ርቀት እንደተጠበቀ እንዲቀጥል
- በአምልኮ ሥርዓት የሚገኙ ምዕመናን ቁጥር ከሕንጻ ቤተክርስቲያኑ ስፋት አንጻር ገደብ ስለሚጥለብን እስከ ፲፭ ሰዎች ብቻ በየአገልግሎቱ እንዲገኙ
- በሰንበተ ክርስቲያን እሑድ ቅዳሴ የምትገኙ ምዕመናን ከሑሙስ አስቀድማችሁ ከዚህ በታች ለተጠቀሱት አንዳቸው እንድታሳውቁ
- አርአያ ገ/ማርያም በስልክ 250-217-6365 ወይም
- ኤርምያስ ኃይሌ በስልክ 778-966-1414
- ሳታስታውቁ የቀራችሁ በዙም በሚተላለፈው መርሃግብር እቤታችሁ አምልኮታችሁን እንድትፈጽሙ። ከላይ የተጠቀሱት አባላትም የምዕመኑን ቁጥር ገደብና አካላዊ ርቀት ቁጥጥር እንዲያደርጉ ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት የመደባቸው መሆኑን እናሳውቃለን።
ይህንን ጊዜ በደህና አሳልፎልን በምልአት ከቅጽረ ቤተ ክርስቲያን አምልኳችንን ለማከናወን እንዲያደርሰን ፈጣሪያችንን እየተማጸንን ለአባታዊ ክትትል፣ ምክርና የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት
- ቀሲስ አበበን በስልክ 778-677-9607 በኢሜይል: chair@stgabrieleotcvictoria.org
ለማኅበራዊ መስተጋብር፣ መረጃዎችና እገዛዎች የክፍሉን ኃላፊ
- ዶ/ር ዮናስን በስልክ 250-813-2056 በኢሜይል: saar@stgabrieleotcvictoria.org እንድታገኟቸው ይሁን።
ልዑል እግዚአብሔር ማኅበራችንን ያስፋልን ይጠብቅልን አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት