እዚህ እንዴት ይመጣሉ?
 • ወደ ቤተ ክርስቲያናችን ለመምጣት ከየትም የዓለም ክፍል ቢሆኑ የጉዞ አቅጣጫዎን ወደ ቢሲ ዋና ከተማዋ ቪክቶሪያ ያድርጉ። እዛ ከደረሱ በኋላ የ፲ ደቂቃ የመኪና ርቀት ነው የሚኖርዎት። ከዚያም
 • በ Johnson St. በመጠቀም ወይም
 • በ Bay St.
 • አሊያም በ Tillicum Rd ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ዋና መንገድ Colville Rd መምጣት ይችላሉ።
 • ለበለጠ መረጃ ከዚህ በታች ያሉትን የአቅጣጫ መጠቆሚያ ተስፈንጣሪዎችን ይመልከቷቸው።
 • የህዝብ ማመላለሻዎች
ስለቤተክርስቲያናችን አካባቢ
    ቅዱስ ገብር ኤል ቤተ ክርስቲያን በስኳይ ማልት ቢሲ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ስኳይ ማልት ደግሞ ከ ፲፫ቱ የታላቋ ቪክቶሪያ (The Greater Victoria) የከተማ አስተዳደሮችና ከ፲፮ቱ የዋና ከተማ ግዛት አስተዳደሮች (Capital Regional District-CRD) ውስጥ የሚገኝ የአውራጃ ከተማ (District municipality) ነው።       በታላቋ ቪክቶሪያ ውስጥ ስኳይ ማልትን ጨምሮ ስምንት የአውራጃ ከተሞች የሚገኙ ሲሆን ሌሎቹ ሦስት ከተሞች (Cities) እና ሁለት ክፍለ ከተሞች (Townships) ናቸው። የታላቋ ቪክቶሪያ ከተማ አስተዳደሮች የአድራሻ መጠሪያ የሆነችውና የካናዳ ክፍለ ሃገር የሆነው የቢሲ ግዛት የመንግስቱ ዋና መናገሻ ከተማ ቪክቶሪያ ነች።     ቤተ ክርስቲያናችን ያለበት የአውራጃ ከተማ፤ ስኳይ ማልት ከምስራቅ ቪክቶሪያ፣ ከሰሜን ሳኒች አውራጃ፣ ከደቡብ የዋን ዲፉካ የግዛቱ ምርጫ ጣቢያ (Strait of Juan de Fuca)፣ ከምዕራብ ደግሞ የቪው ሮያል የአውራጃ ከተማ ያዋስኑታል።
አስተያየትና ጥያቄዎን እዚህ ላይ ይጻፉልን

  የመልአኩ ወዳጆች እንኳን አደረሳችሁ መባዕና ሥጦታዎን እዚህ ላይ ያስገቡ።

  Tithe & Offering, Giving, Thank offering, and others contribution
  X myStickymenu