የቪክቶሪያ ኦርቶዶክስ ምዕመናን የምናመልክበት ህንጻ፣ የሚቀድልን ካህን፣ የምናነግሰው ታቦት አልነበረንም። ከቫንኮቨር ኆኅተ ሰማይ ቅድስት ማርያም ወንድሞች እየመጡ በጸሎት ይራዱን ነበር እንጂ። ለዚህም የምዕመናንን ቤት ጭምር እንጠቀም ነበር። ጊዜው 2008 (እ.ኤ.አ) ለጸሎት ስንጠቀምበት በነበረው 1100 ኮልቪሌ መንገድ ላይ የሚገኘውን የዩክሬናውያን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንን መናገሻ አድርገን በእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ የወንድሞችና የእህቶች ጸሎት ሲሰማ በብጹእ አባታችን አቡነ ማቲያስ መልካም ፈቃድና ቡራኩ የታላቁና ገናናው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ታቦት ገባልን። የደብራችንንም ስም ወደፊት ሊመጣ ስላለው ተገብተው ብጹእ አባታችን ዳግማዊ ቁልቢ መንበረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ብለው ሰየሙት። 

current status and details

ቤተ ክርስቲያኗ ስለሚከተሉት ዓላማዎች ስትል ተቋቁማለች

  • በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት መሰረት በካናዳ ታላቂቷ ቪክቶሪያ ለሚገኙ የቤተ ክርስቲያኗ ተተኪ ትወልድ ከሕፃንነት ጀምሮ መንፈሳዊ ትምሕርትን ፣ግብረገብነትን ፣ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን፣ ባሕላቸውንና ወጋቸውን በማስተማር በመልካም መንፈሳዊ ሥነ ምግባር እነዲታነጹ ለማስተማርና ለማጠንከር፤
  • የቤተክርስቲያኗ አባላት(ምእመናንን) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት(ዶግማ፣ ቀኖና እና ሥርዓት) ጥላ ስር በአንድነትና በፍቅር ተሰባስበው ሃይማኖታቸውን እንዲጠብቁና እምነታቸውን እንዲያስፋፉ ለማድረግ ፤
  • በኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ክርስቲያኑን ማህበረሰብና ተከታዩን ለማጠንከር ይቻል ዘንድ ምእመናኑን በወንጌል ትምህርት ማነፅና የሃይማኖታቸውን መሰረት በማሳወቅ ከሌሎች ጋር በአኩልነት ፣በመከባበር፣ በሰላም ፣በአንድነትና በፍቅር እንዲኖሩ ለማስተማር፤
  • ለአዲስ ስደተኞች ለመቋቋሚያየሚያስፈልጉ ሁኔታዎችን ለማመቻቸትና ለመርዳት፤
  • ለቤተክርስቲያኑ አባላትና እምነቱን ለሚቀበሉ ሁሉ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያንን (ክርስትና ፣ጥምቀት ፣ ጋብቻ፣ ሥርዓተ ቁርባን፣ጸሎተ ፍትሐት፣) ለመፈጸምና መንፈሳዊ ምክር ለመስጠት

የመልአኩ ወዳጆች እንኳን አደረሳችሁ መባዕና ሥጦታዎን እዚህ ላይ ያስገቡ።

Tithe & Offering, Giving, Thank offering, and others contribution
X myStickymenu