"ብቻ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ያዘዛችሁን ትእዛዙንና ሕጉን ታደርጉ ዘንድ፥ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትወድዱ ዘንድ፥ መንገዱንም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ ትእዛዙንም ትጠብቁ ዘንድ፥ ከእርሱም ጋር ትጠጉ ዘንድ፥ በፍጹምም ልባችሁ በፍጹምም ነፍሳችሁ ታመልኩ ዘንድ እጅግ ተጠንቀቁ።" ኢያሱ ፳፪፥ ፭
“ዛሬ በመስታወት በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን ያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን፡፡ አሁን በከፊል ኋላ ግን እንደተገለጠልኝ መጠን ሁሉን አውቃለሁ” (፩ቆሮ ፲፫፥ ፲፪) ብሎ አስተማረን፡፡ ስለዚህም እውቀታችን የተሟላ እንዲሆንና ሰይጣንን ለመቃወም እንድንበቃ የቅዱሳን መላእክት የእውቀት ድጋፍ በእጅጉ ያስፈልገናል፤ ምክንያቱም ከእኛ ይልቅ ሳጥናኤልን የሚያውቁት እነርሱ ናቸውና፡፡ እንዲህም ስለሆነ ጌታችን በእውቀታቸው እኛን እንዲረዱን ለእያንዳንዳችን ጠባቂ መልአክትን ሰጠን፡፡(ማቴ.፲፰፥፲፤ ሉቃ.፲፫፥ ፮-፱)