በመሠራት ላይ ያለ
፬ኛው የቤተ ክርስቲያናችን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ እና ፮ኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ በማዕርገ ጵጵስና የአንድ ዘመን ተሿሚዎች ናቸው፡፡ በሦስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ እድ፣ ጥር ፲፫ ቀን ፲፱፻፸፩ ዓ.ም. ከተሾሙት ፲፫ ኤጲስ ቆጶሳት መካከል ለማዕርገ ፕትርክና የበቁት የዛሬዎቹ ኹለቱ አባቶች ይገኙበታል፡፡ የፊቱ አባ ዘሊባኖስ ፈንታ ብፁዕ አቡነ መርቆሬዎስ ተብለው በኦጋዴን አውራጃ፣ የፊቱ አባ ተክለ ማርያም ዐሥራት ብፁዕ አቡነ ማትያስ ተብለው በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ኤጲስ ቆጶስነት የተሾሙት በአንድ ቀን ነበር፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ፣ ፬ኛ ፓትርያርክ ኾነው የተሾሙት፣ ነሐሴ ፳፱ ቀን ፲፱፻፹ ዓ.ም. ሲኾን፣ መንበራቸውን ለቀው ከሀገር ከመውጣታቸው በፊት እስከ ነሐሴ ፳፰ ቀን ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. ድረስ ለቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ አመራር ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡ ከ፳፮ ዓመታት ስደት በኋላ፣ ሐምሌ ፳፭ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም.፣ በስሙ በተሠየሙበት በሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ክብረ በዓል ወደ ቅድስት ሀገራቸው ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።
በዕርቀ ሰላሙ የጋራ ስምምነት መሠረት፣ ቤተ ክርስቲያናችን፣ የኹለቱንም ቅዱሳን ፓትርያርኮች ስም በጸሎቷ እየጠራች፣ በእኩል የአባትነት ክብር አስቀምጣ በየድርሻቸው እንዲያገለግሏትና እንዲመሯት አድርጋለች፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በጸሎትና ቡራኬ በማድረግ ሲመሯት፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ደግሞ የአስተዳደር ሥራውን በመሥራት ይመሯታል፡፡
ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
በመሠራት ላይ ያለ
ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
በመሠራት ላይ ያለ