፩. ሁሉን በያዘ ሰማይንና ምድርን የሚታይና የማይታየውን በፈጠረ በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን።
፪. ዓለም ሳይፈጠር ከርሱ ጋር በነበረ የአብ አንድ ልጁ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስም እናምናለን።
፫. ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፣ ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ፤ የተፈጠረ ያይደል የተወለደ፤ በመለኮቱ ከአብ ጋር የሚተካከል።
፬. ሁሉ በርሱ የሆነ ያለ እርሱ ግን ምንም የሆነ የለም። በሰማይም ያለ በምድርም ያለ።ስለእኛ ስለሰው ስለ መዳኛችን ከሰማይ ወረደ።
፭. ከመንፈስ ቅዱስ የተነሣ ከቅድስት ማርያም ፈጽሞ ሰው ሆነ።
፮. ሰው ሆኖ በጰንጤናዊ በጲላጦስ ዘመን ስለእኛ ተሰቀለ። ታመመ፤ ሞተ፤ ተቀበረም፤ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፤ በቅዱሳት መጽሐፍት እንደ ተጻፈ።በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ።
፯. ዳግመኛ ሕያዋንን ሙታንንም ይገዛ ዘንድ በጌትነት ይመጣል። ለመንግሥስቱም ፍጻሜ የለውም።
፰. ጌታ ማሕየዊ በሚሆን ከአብ በሠረፀ በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን። እንሰግድለት እናመሰግነውም ዘንድ፤ ከአብና ከወልድ ጋር በነብያት የተነገረ።
፱. ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰብዋት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም እናምናለን።
፲. ኃጥያትን ለማስተሥረይ በአንዲት ጥምቀት አናምናለን።
፲፩. የሙታንንም መነሣት ተስፋ እናደርጋለን የሚመጣውንም ሕይወት ለዘላለሙ አሜን።