በመሠራት ላይ ያለ
የቤተ ክርስቲያንዋ እምነት መርሆዎች
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የዶግማ ትምህርት የተመሠረተው ከመጽሐፍ ቅዱስ ከወጡትና በሦስቱ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች የተደነገጉትን የዶግማ ትምህርቶች ላይ ነው። ዋናዎቹም አምስቱ አእማደ ምሥጢራት ናቸው ።
እነዚህም፤
፩. ምሥጢረ ሥላሴ፣
፪. ምሥጢረ ሥጋዊ፣
፫. ምሥጢረ ጥምቀት፣
፬. ምሥጢረ ቁርባንና
፭. ምሥጢረ ትንሣኤ ተብለው ይጠራሉ።
5.1 ምስጢረ ሥላሴ፣
የምሥጢረ ሥላሴ ትምህርት የአምላክን ሦስትነትና አንድነት የሚያስረዳ ዋና የክርስትና እምነት መሠረት ነው። ይህ ዶግማ ረቂቅ ነው ይህ ትምህርት በእግዜአብሔር ካልተገለጸ በስተቀር በምርምር ብቻ የሚደረስበት አይደለም። “ከአብ በቀር ወልድን የሚያቅ የለም፣ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም።” (ማቴ. 11፥27) የምናመልከው አንድ
አምላክ በባሕሪይ አንድ አካል ሲሆን በግብር ሦስት አካላት ናቸው። ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን የምትቀበለው ይህን ትምህርት ነው “መንፈስም እውነት ነውና የሚመሰክረው መንፈስ ነው። የሚመሰክሩት መንፈሱና ውኃው ደሙም ሦስት ናቸውና ሦስቱም አንድ ናቸው።” (1ኛ ዮሐ. 1፥5-7)
5.2 ምሥጢረ ሥጋዊ፣
ምሥጢረ ሥጋዊ የሚገልጽልን የአምላካችንን የድኅነት ሥራ በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ መገለጹን ነው። ይህም ያስፈለገበት ምክንያት ህመማችን/ቁስላችን ኣዳኝ ሃኪም ስላስፈለገው ነው። (ሉቃ. 19፥10) ጨለማችን ብርሃን ስላስፈለገው ነው። (ማቴ. 4፥12-17፣ ዮሐ. 8፥12) ከባርነት ቀንበር ነጻ የሚያወጣ ስላስፈለገ ነው። (ገላ. 5፥1) በዚህ ጉዳይ ላይ ጸሎተ ሃይማኖትም
አንዲህ ይላል፣ “ስለ እኛ ስለሰው ስለመዳናችን ከሰማይ ወረደ። ከመንፈስ ቅዱስ የተነሣ ከቅድስት ማርያም ፈጽሞ ሰው ሆነ።”
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የምትቀበለው የእስክንድርያውን የቅዱስ ቄርሎስን የዶግማ ትምህርት ነው። “የወልድ አምላክነትን ባሕሪይ” በሌላ አነጋገር ሁለቱ ባሕርያቶች “አምላክነትና ሰውነት” ሲዋሀዱ የክርስቶስ ባሕርይ አንድ ብቻ ነው የሆነው። የቃሉና የሥጋ አንድነት በቅድስት ድንግል ማርያም ማኅፀን ተዋሀደ ስለዚህ የሰውነት ባሕርይም
ለአምላክነት የአምላክነት ባሕሪይም ለሰውነት ይገልጻል። በዚህ ንጹህ በሆነ ተዋህዶ “መለኮትና ሥጋ ያለመቀላቀል ያለመጠፋፋት አንድ ሆነዋልና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ነው” የኽውም ሰው የሆነው አምላክ መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሥጋዊ በኋላ አንድ አካል አንድ ባሕሪይ ያለው ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ነው” ስለዚህ ስለ ሁለት ባሕሪያት
መናገር አይቻልም። ስለዚህም በዮሐንስ ወንጌል እንዲህ ተጽፏል “ቃል ሥጋ ሆነ፣ ጸጋንና አውነትንም ተመልቶ በኛ አደረ፣ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።” (ዮሐ. 1፥14)
የቅዱስ አትናቲዮስ አገላለጽም “አምላክ ሰው ሆነ ይህም የሆነው የሰው ልጅ የሆነውን ወደ አምላክነት እንድንለወጥና የመለኮትን ባሕሪይ ተካፋዮች አንድንሆን ነው።” (2ኛ ጴጥ. 1፥4)
5.3 ምሥጢረ ክርስትና፣
ምሥጢረ ክርስትና ወደ ቤተ ክርስቲያን አባልነት መግቢያ በርና የአምላካችንን የፀጋ ስጦታ የምንካፈልበት ነው። ምሥጢር የተባለበትም ምክንያት የማይታየውን ፀጋ በሚታየው የአምላክ ተግባር ስለምንቀበል ነው። (ማር. 16፥16፣ ዮሐ. 19፥34-35፣ ሐዋ. 2፥38) ። ጥምቀት ወደ ክርስቲያናዊ ሕይወት የሚያስገባን የዕምነት በር ሲሆን ጥምቀት አንድ ጊዜ ብቻ የሚፈጸም እንጂ
በምንም ዓይነት የሚደገም አይደለም። (ኤፌ. 4፥4-7፣ ዮሐ. 3፥3-8)
5.4 ምስጢረ ቁርባን፤
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ባደረገው በመጨረሻው እራት ላይ መሥርቶታል። እንዲህም ብሏል “በዚህ መታሰቢያ ስለ ሞቴና ስለ ትንሣኤዬ አስቡ” (ማቴ. 26፥26-30)
ቅዱስ ጳውሎስም እንዲህ ብሏል “ይህ ጽዋ በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው፣ በጠጣችሁት ጊዜ ሁሉ ይህን መታሰቢያዬን አድርጉት አለ።…” ስለዚህ ለእግዚአብሔር ሳይሰጥ ነገር ግን ስለ ሰዎች ተሰጠ በቁርባኑም ከኃጢያት ተገዢነት የሚያወጣንና ወደ አምላክ የሚያቀርበን ነው። (ዮሐ. 6፥53-57) ቁርባን በመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ልቦና ውስጥ የገባና የመለኮትን ፀጋ ከሰው
ልጅ ሕይወት ጋር የሚያገናኝ ሆነ።
5.5 ምሥጢረ ትንሣኤ፣
ምሥጢረ ትንሣኤ ዓለማዊ ከሆነው ሥጋችን ተለይተን ሞትን ድል አድርገን የምንነሣበትን በኋላም የምናገኘውን ዘለአለማዊ ሕይወት የሚገልጽ ምሥጢር ነው። ይኸውም የሚሆነው የጌታችንና የመድኃኒታች የኢየሱስ ክርስቶስ በክብር መምጣት ሲገለጽ ነው። ልክ እንደማንኛውም ፍሬ መጀመሪያ በስብሶ በኋላ እንደሚያፈራ ሁሉ። (ዮሐ. 12፥24 ፣ 1ኛ ቆሮ. 15፥36) ስለዚህ ሁላችን እንሞታለን
ከዛም እንደገና እንነሣለን የመንግሥቱም ወራሾች ለመሆን። በጸሎተ ሃይማኖትም እንዲህ ይላል “የሙታንንም መነሣት ተስፋ እናደርጋለን፣ የሚመጣውንም ሕይወት ለዘላለሙ አሜን።”