ቃለ ዓዋዲና መተዳደሪያ ደንብ




የሰበካ ጉባኤ መተዳደሪያ ደንብ



የቤተክርስቲያኗ ዓላማዎች
ሀ. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት መሰረት በካናዳ ታላቂቷ ቪክቶሪያ ለሚገኙ የቤተ ክርስቲያኗ ተተኪ ትወልድ ከሕፃንነት ጀምሮ መንፈሳዊ ትምሕርትን ፣ግብረገብነትን ፣ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን፣ ባሕላቸውንና ወጋቸውን በማስተማር በመልካም መንፈሳዊ ሥነ ምግባር እነዲታነጹ ማስተማርና ማጠንከር፤

ለ. የቤተክርስቲያኗ አባላት(ምእመናንን) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት(ዶግማ፣ ቀኖና እና ሥርዓት) ጥላ ስር በአንድነትና በፍቅር ተሰባስበው ሃይማኖታቸውን እንዲጠብቁና እምነታቸውን እንዲያስፋፉ ማድረግ ፤

ሐ. በኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ክርስቲያኑን ማህበረሰብና ተከታዩን ለማጠንከር ይቻል ዘንድ ምእመናኑን በወንጌል ትምህርት ማነፅና የሃይማኖታቸውን መሰረት በማሳወቅ ከሌሎች ጋር በአኩልነት ፣በመከባበር፣ በሰላም ፣በአንድነትና በፍቅር እንዲኖሩ ማስተማር፤

መ. ለአዲስ ስደተኞች ለመቋቋሚያየሚያስፈልጉ ሁኔታዎችን ማመቻቸትና መርዳት፤

ሠ. ለቤተክርስቲያኑ አባላትና እምነቱን ለሚቀበሉ ሁሉ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያንን (ክርስትና ፣ጥምቀት ፣ ጋብቻ፣ ሥርዓተ ቁርባን፣ጸሎተ ፍትሐት፣) ለመፈጸምና መንፈሳዊ ምክር ለመስጠት

የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የመተዳደሪያ ደንብና ህግ ፪ኛ እትም

 

 

የመልአኩ ወዳጆች እንኳን አደረሳችሁ መባዕና ሥጦታዎን እዚህ ላይ ያስገቡ።

Tithe & Offering, Giving, Thank offering, and others contribution
X myStickymenu