የቀደሙ በዐላት ተንቀሳቃሽ ምስሎች እዚህ ላይ ያገኛሉ For previous celebration videos
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እናምናለን።አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እናምናለን።
ሁሉን በያዘ ሰማይንና ምድርን የሚታየውንና የማይታየውን በፈጠረ በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን።
ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ ጋር በነበረ የአብ አንድ ልጅ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን። ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፤ ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ፤ የተፈጠረ ያይደለ የተወለደ፤ በመለኮቱ ከአብ ጋር የሚተካከል። ሁሉ በእርሱ ሆነ ያለ እርሱ ምንም ምን የሆነ የለም፤በሰማይም ያለ በምድርም ያለ። ስለ እኛ ስለ ሰዎች ስለመዳናችን ከሰማይ ወረደ።
በመንፈስ ቅዱስ ግብር ከቅድስት ድንግል ማርያም ፈጽሞ ሰው ሆነ። ሰው ሆኖ በጰንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን ስለእኛ ተሰቀለ፤ታመመ፤ ሞተ፤ ተቀበረ፤
በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፤ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈ። በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ። ዳግመኛም ሕያዋንንና ሙታንንም ይገዛ ዘንድ በጌትነት ይመጣል።ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም።
ጌታ ማኅየዊ በሚሆን ከአብ በሰረፀ በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን፤ እንሰግድለት እናመሰግነውም ዘንድ ከአብና ከወልድ ጋር በነቢያት የተናገረ።
ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰብዋት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን። ኃጢአትን ለማስተሥረይ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን። የሙታንንም መነሣት ተስፋ እናደርጋለን። የሚመጣውንም ሕይወት ለዘለዓለሙ አሜን።
ዜናና በዓላትማስታወቂያዎች
የዐብይ ጾም
መልዕክታት የመጀመሪያውን
ቅጽ ያንቡ
መጽሐፈ ግጻዌን እዚህ ላይ ይመልከቱ
“እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና “እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና
እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ በደስታ ይስጥ” ፪ኛ ቆሮ ፱፥፯
ስለ እኛ
“የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን” ዮሐ ፫፥ ፲፩
የቪክቶሪያ ኦርቶዶክስ ምዕመናን የምናመልክበት ህንጻ፣ የሚቀድልን ካህን፣ የምናነግሰው ታቦት አልነበረንም። ከቫንኮቨር ኆኅተ ሰማይ ቅድስት ማርያም ወንድሞች እየመጡ በጸሎት ይራዱን ነበር እንጂ። ለዚህም የምዕመናንን ቤት ጭምር እንጠቀም ነበር። ጊዜው 2008 (እ.ኤ.አ) ለጸሎት ስንጠቀምበት በነበረው 1100 ኮልቪሌ መንገድ ላይ የሚገኘውን የዩክሬናውያን ቅዱስ ጊዮርጊስ
ቤተ ክርስቲያንን መናገሻ አድርገን በእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ የወንድሞችና የእህቶች ጸሎት ሲሰማ በብጹእ አባታችን አቡነ ማቲያስ መልካም ፈቃድና ቡራኩ የታላቁና ገናናው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ታቦት ገባልን። የደብራችንንም ስም ወደፊት ሊመጣ ስላለው ተገብተው ብጹዕ አባታችን ዳግማዊ ቁልቢ መንበረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ብለው ሰየሙት።
የቤተ ክርስቲያን አገልግሎቶች
- በቅዱስ ገብርኤል ወርሃዊ ቀን
- በበዓላት፣ አጽዋማት ወቅትና በቀዳሚት ሰንበት (ቅዳሜ)
- በክርስቲያኖች ሰንበት
- አበይት በዓላት ወቅት
- የሰንበት ትምህርት ቤት መርሃ ግብር
ጸሎተ ኪዳንና ሌሎች ጸሎታት ጠዋት ከ 5:00 AM ጀምሮ
ትምህርትና ዝክር ማታ ከ 6:00 PM ጀምሮ
ጸሎተ ቡራኬ፣ ጸሎተ ኪዳን፣ ስብከት ጠዋት ከ
5:00 AM ጀምሮ
ቅዳሴ (ታላላቅ በዓላት በዋሉ ጊዜ) ጠዋት 8:00 AM የከሰዓት ቅዳሴ 1:00 PM
ሰዓታት ወይም ማኅሌት ጸሎት ጠዋት 5:00 AM (በበዓላት ወቅት 4:00 AM ይጀምራል)
የክርስትና ጥምቀት ጠዋት 6:00 AM
የኪዳን ጸሎት ጠዋት 7:00 AM
የቅዳሴ ጸሎት ጠዋት 8:00 AM ይጀመራል (በአበይት በዓላት ከ 6:00 AM ይጀመራል)
ዝማሬና ስብከት ረፋድ 11:00 AM እስከ 12:00 PM
ዋዜማ ከሰዓት 4:00 PM
የሰዓታትና ማኅሌት ጸሎት ጠዋት 2:00 AM
የክርስትና ጥምቀት ጠዋት 5 :00 AM
የኪዳን ጸሎት ጠዋት 5:30 AM
የቅዳሴ ጸሎት ጠዋት 6:00 AM ይጀመራል
ዝማሬ፣ ስብከትና የታቦት ንግስ ረፋድ 9:00 AM እስከ 12:00 PM
በሰሙነ ሕማማት (ከሰኞ እስከ አርብ) ጠዋት 6:00 AM እስከ እስከ 12:00 PM
በጾመ ፍለሰታ (ሙሉውን ጾም) ሰዓታት፣ ኪዳንና ትርጓሜ ንባባ ጠዋት 6:00 AM ጅምሮ
ህጻናት ከ ፫ዓመት እስከ ፯ ዓመት በየሳምንቱ እሑድ ረፋድ 11:00 AM እስከ 12:00
ታዳጊዎች ከ፯ ዓመት በላይ በየሳምንቱ ቅዳሜ ከሰዓት ከ4:00 PM እስከ 6:00 PM